ስለ እኛ
ኢትዮ-አጋፔ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት (ኢአመጥ)
እኛ የኢትዮ አጋፔ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ወንድሞች እና እህቶች በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰላምታ እናቀርብላችኋለን!
ሕይወታችንን የለወጠውን የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምሥራች በማካፈል የቻልነውን ያህል ልናገለግልዎት
እንፈልጋለን እናም በእናንተም ላይ እንዲሁ እንዳደረገ ወይም እንደሚያደርግ እናውቃለን። እኛ የኢትዮጵያ ሰባተኛ ቀን
አድቬንቲስት ቤተክርስቲያን አባላት ነን እና ከቤተክርስቲያን ቢሮዎች ጋር በቅርበት ግንኙነት እና ትብብር እንሰራለን።
በቂ ዝግጅት እስክናደርግ ድረስ ሙሉ በሙሉ “በቤተ ክርስትያን የተመሰረተ የወንጌል አገልግሎት” የሚል ዕውቅና
እንዲሰጠን ቤተ ክርስቲያናችንን አልጠየቅንም ስለዚህም አልተሰጠንም።
በዚህ መሰረት፣ በአሁኑ ወቅት ምንም ዓይነት የገንዘብ/ቁሳቁስ ድጋፍ የማንሰበስብ ሲሆን በጸሎት እንድትደግፉን
እየጠየቅን ለኦዲዮቪዥዋል ዝግጅቶቻችን ማጠናከሪያ፣ ለተለያዩ የትርጉምና ህትመት ስራዎች . . . ድጋፍ
ልታደርጉልን ብትሹም ደግሞ ለእኛ አገልግሎት ድጋፉን ገቢ የምታደርጉበትን የቤተ ክርስቲያን የሂሳብ ቁጥር ልንሰጣችሁ
እንደምንወድ ልንገልጽላችሁ እንወዳለን – አግኙን። በአብዛኛው እስካሁን የምንሰራው በማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች
ላይ እንደመሆኑ መጠን በማህበራዊ ሚዲያ አድራሻችን ላይ የሚለቀቁት ኦዲዮቪዥዋል እንዲሁም ሌሎች ስራዎች
እንዲደርሷችሁ ሰብስክራይብ፣ ላይክ . . . እንድታደርጉ እና ሲደርሷችሁም ለብዙዎች በማጋራት አብረን
እንድናገለግል በጌታ ፍቅር እንጠይቃችኋለን።
ጌታ ይባርካችሁ!
ጌታ ይባርካችሁ!
"በምድርም ለሚኖሩ ለሕዝብም ለነገድም ለቋንቋም ለወገንም ሁሉ ይሰብክ ዘንድ የዘላለም ወንጌል ያለው ሌላ መልአክ በሰማይ መካከል ሲበር አየሁ።"
የዮሐንስ ራእይ 14:6